News Detail

ገጽታ
Oct 29, 2025 184 views

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል የ2018 1ኛ ሩብ ዓመት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ፤

ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት (ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም)

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል የ2018 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል፡፡የሪፖርት ግምገማውን በንግግር ያስጀመሩት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ድሪባ ኢትቻ ሲሆኑ የሪፖርት ግምገማው ዋና ዓላማ የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸማችንን በመገምገም ያላሳካናቸው ተግባራት ካሉ በ2ኛው ሩብ ዓመት ላይ የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያስችለን እና ተሰርተው ነገር ግን በሪፖርቱ ያልተካተቱ ጉዳዮች ካሉ እንዲካተቱ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሪፖርቱን ሊያዳብሩ የሚችሉ ሀሳብና አስተያዮቶችን ለማሰባሰብ አዲቻል ነው ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ባለፈው 2017 በጀት ዓመት ዩኒቨርሲቲው በስኬት ያከናወናቸውን ዓበይት ተግባራት ዘርዘር አድርገው ለካውንስሉ በማቅረብ ዓመቱ የስኬት ዓመት እንደነበር በመጥቀስ ያላሳካናቸው እና በውስንነት ከታዩ አፈጻጸሞች ትምህርት በመውሰድ በያዝነው 2018 በጀት ዓመት በበለጠ ስኬት እንድናጠናቅቃቸው የሁላችንም ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የ2018 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን አጠናቅረው ያቀረቡት የእስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ኡቻን ኡኬሎ ሲሆኑ በቀረበው ሪፖርት ጋር ተያይዞ ለቀረቡ ጥያቄዎች የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

መምህራን ሲቀጠሩም ሆነ ወደ ኃላፊነት ሲመጡ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው እና ተወዳድረው እንደሆነ የገለጹት ዶ/ር ፓል መምህራን በመማርና ምርምር በመስራት ፐሮፊላቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

እተከናወነ ያለው የውስጥ ገቢ ማመንጫ የእርሻ ስራ ፣ ስለግቢው ሰላምና ጸጥታ እና የጥገና ስራዎች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮናስ ከፍያለው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የእርሻ ስራው የአካባቢው አርሶ አደሮች ልምድ ሊወስዱበት የሚገባ ዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴን መከተል አለበት ካሉ በኋላ በተለይ የግብርና ኮሌጅ ይህንን የውስጥ ገቢ ማመንጫ ስራ ሊመራው እንደሚገባና በዚህ ረገድ ሁሉም መተባበር እንዳለበት ዶ/ር ዮናስ ገልጸዋል፡፡ የውስጥ ገቢ ማመንጫ ሰራተኞች የውስጥ ገቢውን ስራ በመቆጣጠር ስራ ላይ እንዲሰማሩ እንጂ በእርሻ ስራው ላይ ቀጥታ መሳተፍ እንደሌለባቸውም በአጽንዖት ተናግረዋል፡፡

ከግቢው ጸጥታ ጋር ተያይዞ ለቀረበው ጥያቄ ዶ/ር ዮናስ ሲመልሱ እየተዘረጋ ያለው የሲሲቲቨ ካሜራ ሲጠናቀቅ የግቢውን የሰላም እና ደህንነት ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ይቀርፋል ብለዋል፡፡ የጥገና ስራዎች በዕቅድ ተይዘው መሰራት እንዳለባቸው ገልጸው የስራ ክፍሎች የጥገና ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅጥ አፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል፡፡

የትምህርት ጥራትን በማሻሻል፣ የተማሪዎችን መሰረታዊ አገልግሎት በማሟላት፣ ግቢያችንን አረንጓዴና ጽዱ በማድረግ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲያችንን በማስተዋወቅ በተማሪዎች ዘንድ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ እንድንሆን ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል ሲሉ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መልዕክ አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም የጋራ ዓላማና ተነሳሽነት እንዲኖረን በቀጣይ ቀናት ከሰራተኞች ጋር ውይት እንደሚደረግ ገልጸው የዩኒቨርሲቲያችን የልየታ ሰነድ ከተጠናቀቀ በኋላ በያዝናቸው የትኩረት መስኮች ላይ ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡

Recent News
Follow Us